ስለ እኛ

 
 
ፕሮጀክቱ ማንን ይደግፋል?
  • እንደ ዓለም አቀፍ ሙያተኛ ወደ ጀርመን መምጣት ይፈልጋሉ? 
  • በጀርመን ሃገር የሙያ ሥልጠና ማከናወን ይፈልጋሉ?
  • እጮኛዎ ወይም ባለቤትዎ በጀርመን ይኖራሉ?
  • በጀርመን ውስጥ ከእሱ / እሷ ጋር መኖር ይፈልጋሉ?
  • ከጀርመን የትዳር ጓደኛዎ ወይም ከጀርመን ልጅዎ ወይም ከጀርመን ወላጅዎ ጋር ወደ ጀርመን መሄድ ይፈልጋሉ?
  • ቀድሞውኑ በጀርመን ውስጥ ይኖራሉ እና ለአካለ መጠን ያልደረሰው ልጅዎ በጀርመን ውስጥ እንዲኖር ይፈልጋሉ
ትክክለኛ ቦታ ነዎት
ይህ ፕሮጀክት ወደ ጀርመን ለሚያደርጉት "ህጋዊ እና ስኬታማ ጉዞ "  እርሶን መደገፍ ይችላል ሊደግፎትም ይወዳል.
ለዚሁ ዓላማ በኢትዮፒያ በአልባኒያ በአርሜኒያ በቦስኒያ-ሄርዞጎቪና በጆርጂያ በኮሶቮ በሩሲያ በቱርክ እና በዩክሬን ፕሮጀክቱ ምክር አገልግሎት ቢሮ ያለውና ለተጠቃሚዎች አስፈላጊውን ማህበራዊና-ትምህርታዊ መረጃዎችን በቡድን እና ግለሰብም ምክር ሚሰጡ ባለሙያዎች አቋቁመዋል። ምክር አገልግሎቱ ከክፍያ ነፃ ነው

 


ፕሮጀክቱ እርሶን እንዴት ሊደግፎት ይችላል?
ፕሮጀክቱ በዋነኝነት የሚያተኩረው በማማከር ላይ ነው። ወደ ጀርመን ሊያደርጉ ላቀዱት ጉዞ የሚያስፈልጎትን መረጃ ሁሉ ከእኛ ሊያገኙ ይችላሉ። በቪዛ ሂደት፣ መሆን እና መደረግ ያለባቸውን ዝርዝር ጉዳዮችንና ወደፊት በጀርመን ውስጥ ለሚኖሮት ሕይወት በተሻለ ሁኔታ እንዲያዘጋጁ እናማክሮዎታለን እንረዳዎታለን።
ጀርመን ከደረሱም በሃላ በዚያ ከሚገኙ የስደተኞች የምክር አገልግሎት ማዕከላት (ካሪታስ ፣ ዳያኮኒ ፣ AWO ፣ DRK፣ ፓሪቲሽቸር ዎልፋህርትስባንድ) ተጨማሪ ድጋፍ እና መመሪያ ያገኛሉ። አላማችን ሁል ጊዜ አስፈላጊ የሆነውን  ምክር እና ድጋፍ ሁሉ እንዲያገኙ ነው።
በፕሮጄክታችን የሚሰጡ የምክር አገልግሎቶች ፣ የሚያተኩሩት የቪዛ ና ተያያዥ ከመኖሪያ  መብቶችና ጉዳዮች፣እንደ  የጀርመንኝ ቋንቋን የመማር፣ ከፍተኛ ትምህርት ና የሙያ ስልጠና ለማግኘት የሚያስችሉ ሲሆኑ ። በተጨማሪም  ስለ ኑሮ ሁኔታና ተዛማጅነተ ያላቸው ስለ ወጪ፣ ህክምና ስለ መሳሰሉ አጠቃላይ ምክር የሚሰጡ ማዕከሎችና ስለ ጀርመን ከሚደረጉ ሌሎች ተያያዥ መረጃዎች ጋር በተያያዘ አስተማማኝ መረጃ ያገኛሉ። 

በዚህ ምክር መሠረት ወደ ጀርመን ለመሂድ የወሰነ ማንኛውም ሰው እዚያ ምን እንደሚጠብቅ ፣ ምን መብቶች ፣ ግዴታዎች እና እድሎች እንዳሉት እና እንደሌሉት ያውቃል።
እርሶም በደንብ ተዘጋጅተው ወደ ጀርመን በመምጣት ስኬታማ ይሆኑ።
ቪድዮ 1 የስራ ና የሙያ ስልጠና ለሚፈልጉ የውጭ ሃገር ባለሙያዎችን የሚመለከተውን አዲሱንና የተሻሻለውን የጀርመንን ህግ የሚያብራራ  
 

 
 
Bitte beachten Sie:
Bitte beachten Sie, dass diese Informationen eine individuelle Beratung nicht ersetzen können. Bitte wenden Sie sich an die Projektmitarbeiter*innen und an die zuständigen Migrationsberatungsstellen. Die Beratung ist kostenlos. Weitere Infos zum Thema Migration - insbesondere ausführliche rechtliche Informationen - finden Sie hier